የጽ/ቤቱ ኃላፊ መልእክት

የሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት በከተማው አስተዳደር ምክር ቤት አዋጅ ቁጥር 74/2014 በከተማዋ ዘላቂና አስተመማማኝ ሰላምና ጸጥታ እንዲሰፍን የማረጋገጥና ተልዕኮ ተሰጥቶት የተቋቋመ ተቋም ነው፡፡ በዚሁ መሰረት ጽ/ቤቱ የተሰጠውን ተግባርና ኃላፊነት ውጤታማ በሆነ መልኩ ለመወጣትና ያስቀመጠውን ራዕይና ተልዕኮ ለማሳካት በየጊዜው አዳዲስ አሠራሮችንና የለውጥ መሳሪያዎችን በስራ ላይ በማዋል ከጊዜ ወደ ጊዜ በመዋቅሩ ላይም ሆነ በአሰራርና በአመለካከት ላይ ለውጦች እንዲመዘገቡ ጥረቶች ሲያደረግ ቆይቷል፡፡

በዚህም የተቋሙ አገልግሎት ለዜጎች ተደራሽ እንዲሆን ከማዕከል እስከ ወረዳ ያሉትን አሠራርና አደረጃጀቶች እንደገና በማጤን አገልግሎት አሰጣጡ ይበልጥ የተቀላጠፈ እንዲሆን በሰው ሀይልና በግብዓት አቅርቦት የተሟላ በማድረግና እንዲሁም በአገልግሎት አሰጣጡ ላይ የሚታዩ የመልካም አስተዳደርና የብልሹ አሰራር ችግሮችን በተቀናጀና በተደራጀ የህብረተሰብ ተሳትፎ ደረጃ በደረጃ በመቅረፍ ሴክተሩ አሁን ለደረሰበት ደረጃ የበኩሉን አስተዋፅኦ አበርክቷል፡፡ በመሆኑም በቀጣይ ጊዜያት ሴክተሩ ከተቋቋመለት ዓላማ አንፃር የህብረተሰቡን ሁለንተናዊ ተሳታፊነትና የሰላም ባለቤትነት ለማረጋገጥ በተለይም ህዝቡ የዚህ ዓላማ ባለቤት እንደመሆኑ መጠን በሚደረገው ሁለንተናዊ እንቅሰቃሴዎች ውሰጥ የማይተካ ሚና አለው ፡፡

ዶ/ር ጥበቡ ደጀኔ , የአዲስ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ
image description