ዜና | Oduu | News
የጥምቀት በዓል ሐይማኖታዊ ትውፊቱ ተጠብቆ በሰላም እንዲጠናቀቅ በክፍለ ከተማው የተደረገው የቅድመ ዝግጅት ስራ የሚደነቅ ነው:: ወ/ሮ አለምፀሐይ ሽፈራው: - የአዲስ አበባ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅርጫፍ ጽ/ቤት ምክትልና ፖለቲካ ዘርፍ ሃላፊ

የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ አስተዳደር የከተራና የጥምቀት በዓል አከባበር ቅድመ ዝግጅት ሥራዎችን በተመለከተ የከተማ ደጋፊ አመራሮች እንዲሁም የክፍለ ከተማና የወረዳ አመራሮች በተገኙበት ተገምግሟል:: መድረኩን የመሩት የአዳስ አበባ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ምክትልና ፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ ወ/ሮ አለምፀሐይ ሽፈራው የጥምቀት በዓል ሐይማኖታዊ ትውፊቱ ተጠብቆ በሰላም እንዲጠናቀቅ በክፍለ ከተማው የተደረገው የቅድመ ዝግጅት ስራ የሚደነቅ መሆኑን ጠቅሰው፣ በበዓሉ አከባበር ላይ በዓሉን የማይመጥኑና በህግ የተከለከሉ ነገሮችን በዓሉ ወደ ሚከበርባቸዉ ቦታዎች ይዞ አለመገኘት እና በዓሉ በድምቀት ተከብሮ እንዲያልፍ ለማስቻል አመራሩ ከፀጥታ ኃይሉ ጋር ተቀናጅቶ በመስራት ኃላፊነቱን በጥብቅ ዲሲፕሊንና በብቃት እንዲወጣ አጠንክሮ መሥራት ይገባል ብለዋል። የአዲስ ከተማ ክ/ክፍለ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ታረቀኝ ወርቅነህ በበኩላቸው በዓሉ ሰላማዊ ሆኖ እንዲከበር አስፈላጊው የቅድመ ዝግጅት ስራ ተጠናቅቆ ወደ ተግባር መገባቱን አስታውቀዋል:: የክፍለ ከተማው ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዘሪሁን ኮርሜ በበኩላቸው ወጣቶችና ህብረተሰቡ ከፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት በዓሉ በሰላም እንዲጠናቀቅ ሰፊ ስራ የተሰራ ሲሆን በዚህም ከተለያዩ የህዝብ አደረጃጀትና የፀጥታ አካላት እንዲሁም መላው ህዝባችን ጋር ውይይት መደረጉን አስታውሰው፤ ህብረተሰቡ ከአጠቃላይ ፀጥታ አካላት ጋር እጅና ጓንት በመሆን በዓሉ በድምቀት እንዲከበር የበኩሉን ሚና እንዲወጣ የሚያስችል ስራ መሰራቱን ገልጸዋል። የአዳስ አበባ ከተማ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ አወሉ መሐመድ በበኩላቸው በዓሉ ሐይማኖታዊ ሥነ ሥርዓቱንና ትውፊቱ ተጠብቆ እንዲከበር እና ለጋራ ደህንነት ሲባል የፀጥታ ኃይሉ ለሚያከናውነው የፀጥታ ስራ ህብረተሰቡ ተባባሪነቱን አጠናክሮ እንዲቀጥል አስገንዝበዋል። በመድረኩ የክፍለ ከተማው ሰላምና ፀጥታ ኃላፊ ዶ/ር ጥበቡ ደጀኔ እስካሁን የተሰሩ ስራዎችንና የወደፊት አዝማሚያዎችን የሚያስቃኝ መወያያ ሰነድ አቅርበዋል::

image
image
image
image
ዜና | Oduu | News
የአካባቢን ሰላምና ደህንነት ለማረጋገጥ የሰላም ሠራዊት አባላት አይተኬ ሚና እንዳላቸው ተገለፀ::

በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ከሁሉም ወረዳ አዲስ ለተመለመሉ የሠላም ሠራዊት በሰላምና ፀጥታ ትግበራ ዙሪያ የንድፈ ሀሳብና የክህሎት ስልጠና ተሰጥቷል:: የመድረኩ መክፈቻ ንግግር ያደረጉት የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ታረቀኝ ወርቅነህ የክፍለ ከተማችንን ሠላምና ፀጥታ ለማስፈን የሠላም ሠራዊት አይተኬ ሚና እንዳላቸው ባለፉት ሥራ ላይ በነበሩት የሠላም ሠራዊት ሁሉ አቀፍ የሠላምና ፀጥታ ሥራዎችን ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ቁርና ፀሐይ ሳይበግራቸው ሲሰሩ ቆይተዋል፤ በመሆኑም ዛሬ የሚሰጠውን የሠላም ሠራዊት ንድፈ ሀሳብና የክህሎት ስልጠና በትኩረት በመከታተል ሰልጥናችሁ ለአካባቢያችን የተረጋጋና ከተለያዩ የወንጀል ድርጊት የፀዳ ተግባር ማከናወን ይጠበቅባችኋል ሲሉ አስገንዝበዋል። የአዲስ አበባ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ብርሃኑ ረታ በበኩላቸው ክፍለ ከተማው የሀገራች ትልቁ የክፍት ገበያ መርካቶ መገኛ እና የሀገራችን የንግድ ማቀላጠፊያ የጀርባ አጥንት አካባቢ እንደመሆኑ መጠን የገበያ እንቅስቃሴውን ሰላማዊና የተረጋጋ ለማድረግና ሌሎችንም የፀጥታ ሥራዎችን ከመደበኛ የፀጥታ አካላት በተጨማሪ የሠላም ሠራዊት ጉልህ አስተዋጽኦ በማበርከታቸው አዲስ ለተመለመሉ የሠላም ሠራዊት የንድፈ ሀሳብና የክህሎት ስልጠና እንደሚሰጥ ገልጸዋል። የክፍለ ከተማው ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ ዶ/ር ጥበቡ ደጀኔ በበኩላቸው ከሁሉም ወረዳ አዲስ ለተመለመሉ የሠላም ሠራዊት በሰላምና ፀጥታ ትግበራን አስመልክቶ የንድፈ ሀሳብና የክህሎት ስልጠና በተጨማሪ በቀጣይ ባሉት ቀናት የአካል ብቃት፣ የስነ ልቦና ቁርጠኝነት እንዲሁም ጥብቅ የሠላም ሠራዊት ዲሲፕሊን ሥነ ምግግ እንደሚሰጥ ተናግረዋል። በክፍለ ከተማው ፖሊስ መመሪያ የወንጀል መከላከልና ማህበረሰብ አቀፍ ኃላፊ ዋና እንስፔክር ጳውሎስ ተመስገን በበኩላቸው ወንጀልን አስቀድሞ ለመከላከል በእንቅስቃሴ ውስጥ የማስተወል ጥበብንና ትኩረት ሰጥቶ በመሥራት ሚያደርሰውን ጉዳት መቀነስ እንደሚቻልና የአካባቢን ሰላም፣ ደኅንነትና ጥቅም መጠበቅና ማረጋገጥ ይገባናል ሲሉ አስገንዝበዋል። የጽ/ቤቱ የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ አስተባባሪ አቶ አምባዬ ወ/ማርያም በበኩላቸው 6ኛ ኮርስ ለአዲስ የሠላም ሠራዊት ተመልማይ የንድፈ ሀሳብና የክህሎት ስልጠና እንዲሁም በሠላም ሠራዊት መተዳደሪያ ደንብ የተዘጋጁ ሰነዶችን በዝርዝርና በስፋት አቅርበዋል። ከላይ ከተጠቀሱት ኃላፊዎች በተጨማሪ የክፍለ ከተማው ፖሊስ መመሪያ ዋና አዛዥ ኮሚሽነር መኮነን አሻግሬና የፖሊስ ባልደረቦቹ እና የወረዳ የሰላምና ፀጥታ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

image
image
image
image
ዜና | Oduu | News
በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ በባለ ጉዳይ ቀን እየተሰጠ ያለው አገልግሎት ተጠናክሮ ቀጥሏል::

በክፍለ ከተማ አስተዳደሩ በባለጉዳይ ቀን የተቀናጀ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ለተገልጋዮች ምላሽና ማብራሪያ እየሰጠ ይገኛል:: በሌሎች ተቋማትም የሚሰጠው አገልግሎት ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን የሴክተር ተቋማት አመራሮችና ባለሙያዎች ተገልጋዮችን በማስተናገድ ላይ መሆናቸውን የኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ባደረገው ምልከታ ተረጋግጧል::

image
image
image
image
ዜና | Oduu | News
በህብረተሰብ ተሳትፎ ሥራ ፍትሐዊ የፋይናንስ አሰባሰብን ለማረጋገጥ እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ።

የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ህብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ከሁሉም ወረዳ ለተውጣጡ የቅጥር ጥበቃና የኮሚኒት ፖሊስ አባላት በቅጥር ጥበቃ መመሪያ 144/2016 እና በፋይናንስ መመሪያ 20/2015 የግንዛቤ ማስጨበጫ ውይይት አካሂዷል። መድረኩን የመሩት የክ/ከተማው ህብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሪት ሐብታሟ ቡልቻ በህብረተሰብ ተሳትፎ ሥራ ፍትሐዊ የፋይናንስ አሰባሰብን ለማረጋገጥና የሐብት ብክነት እንዳይሰት ለመከላከል በቅጥር ጥበቃ መመሪያ 144/2016 እና በፋይናንስ መመሪያ 20/2015ን በመከተል በትክክል እንዲሠራበት የሚታዩ የክህሎት ክፍተቶችን ለመሙላት እንዲረዳ የተሰጠ የግንዛቤ ማስጨበጫ ነው ብለዋል። የክፍለ ከተማው ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ ዶ/ር ጥበቡ ደጀኔ በበኩላቸው የህብረተሰቡን ሰላምና ደህንነት በአስተማማኝ ሁኔታ ለመጠበቅ የቅጥር ጥበቃ አደረጃጀት ሁነኛ ድርሻ እንዳለው ገልጸዋል። በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ፖሊስ መመሪያ የማህበረሰብ አቀፍ ኃላፊ ዋና ኢንስፔክተር ጳውሎስ ተመስገን በበኩላቸው የነዋሪዎችን ሁሉንተናዊ ደህንነትና እንቅስቃሴ ሰላማዊ መንፈስ ለመፍጠር በህዝብ አጋዥነት እየተሠራ መሆኑን ተናግረዋል። የውይይቱ ተሳታፊዎች በበኩላቸው የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነትና የህዝብ አደራን በአግባቡ ለመወጣት ጠንክረው እንደሚሠሩ ገልጸዋል።

image
image
image
image
ዜና | Oduu | News
ለግል ጥበቃ ኤጀንሲዎች፣ ለኮንዶሚኒየምና ለማህበር ቤት ጥበቃዎች በወንጀል መከላከልና መቆጣጠር ዙሪያ የአቅም ግንባታ ስልጠና ተሰጠ።

የአዲስ አበባ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ፣ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን፣ የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት፣ ከፌደራል ፖሊስና ከአዲስ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ጋር በመተባበር ለፌዴራል ፓሊስ አባላት፣ ለግል ጥበቃ ኤጀንሲዎች፣ ለቅጥር ጥበቃ አባላት፣ ለኮንዶሚኒየምና ለማህበር ቤቶች ጥበቃዎች በወንጀል መከላከልና መቆጣጠር ሲስጥ የቆየውን የአቅም ግንባታ ስልጠና አጠናቀዋል። መድረኩን የመሩት በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ ዶ/ር ጥበቡ ደጀኔ የወንጀል ድርጊቶችን አስቀድሞ በመከላከል በዜጎችና ሀገር ላይ የሚደርሰውን ጉዳት ለመቀነስ የሁሉንም የተቀናጀ ጥረት የሚጠይቅ መሆኑን ጠቅሰው፤ በቅርበት ከህብረተሰቡ ጋር ለመሥራት የተለያዩ የኤጀንሲዎችንና የተቋማትን ንብረት ከስርቆት ለመጠበቅ ሲባል የወንጀል መከላከል ስትራቴጂውን የማስገንዘብና በወንጀል መከላከል ስራ ከህብረተሰቡ ጋር እንዴት በጋራ እንደሚሰራ ግንዛቤ ለማስጨበጥ ታላሚ ያደረገ ስልጠና መሆኑን ተናግረዋል ። በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ፓሊስ መምሪያ የወንጀል መከላከል ምክትል ዳይሬክተር ኮማንዶር ተስፋዬ ደገፋ በበኩላቸው የወንጀል መከላከል ፈፃሚዎች አቅም ማጎልበት ለዘላቂ ሰላም መስፈን ጠንካራ የፍትሕ ስርዓት እንደሚረጋገጥ እና በወንጀል መከላከል ውስጥ ህብረተሰቡን ካልያዝን ወንጀል መከላከላችን ውጤታማ አይሆንም ሲሉ ባቀረቡት ሰነድ ገልጸዋል ። በፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ጽ/ቤት የግል ጥበቃ አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች ቁጥጥርና ፈቃድ ከፍተኛ ባለሙያ ኢንስፔክተር ሙሉጌታ ገላው በበኩላቸው ለፌዴራል ፓሊስ አባላት፣ የቅጥር ጥበቃና ለግልና ለተቋማት ጥበቃዎች በወንጀል መከላከልና መቆጣጠር የአቅም ግንባታ ስልጠና መስጠት ወንጀልን ሙሉ በሙሉ ማጥፋት ባይቻልም አስቀድሞ በመከላከል የሚያደርሰውን ጉዳት መቀነስ እንደሚቻልና የተቋማትን ሰላም፣ ደኅንነትና ጥቅም መጠበቅና ማረጋገጥ መቻሉ ሥራዎችን ስልታዊና ቴክኒካል ባለው እውቀትና ክህሎት እንዲመራና ወንጀልን አስቀድሞ ለመከላከል ይረዳናል ሲሉ በማስገንዘብ የእለቱ የስልጠና መድረክ ተቋጭቷል።

image
image
image
image
ዜና | Oduu | News
የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ አስተዳደር የፀጥታ ጥምር ግብረ ኃይል ወቅታዊ የፀጥታ ሥራዎችን ገመገመ።

የክፍለ ከተማው የፀጥታ ጥምር ኃይሉ ሁሉም የፀጥታ ጥምር ግብረ ኃይል አባላት በተገኙበት ትኩረት በሚሹ ወቅታዊ የፀጥታ ሥራዎችን በጥልቀት ገምግሟል። መድረኩን የመሩት የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ዋና ሥራ አስፈፃሚና የጥምር ኃይሉ ሰብሳቢ አቶ ታረቀኝ ወርቅነህ ጥምር ኃይሉ የተሠሩ ወቅታዊ የፀጥታ ሥራዎችን በአግባቡ ከተለያዩ ተቋማት ጋር በቅንጅት ሥራዎችን ለሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ተልዕኮና ሥምሪት በመሥጠት የክፍለ ከተማውን ሰላምና ደህንነት በአስተማማኝ ሁኔታ መጠበቅና ነዋሪዎችን በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴው ተረጋግቶ እለት ተዕለት ተግባሩን እንዲያከናውኑ ሁላችንም ኃላፊነታችንን እንወጣ ሲሉ አሳስበዋል። የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ብርሃኑ ረታ በበኩላቸው ወቅታዊ የፀጥታ ሥራዎችን ለማከናወን ሰላምና ደህንነትን ማረጋገጥ የሚቻለው የፀጥታ ኃይሉ ከህብረተሰቡ ጋር ተቀናጅቶና ተናቦ ሲሰራ መሆኑን ጠቅሰው፤ የአፍራሽ ኃይሉን ከፋፋይ አጀንዳዎችንና ህገ ወጥ ተግባራትን በመከላከል ረገድ የሰላም ሰራዊት አባላትና ህብረተሰቡ የበኩሉን ሚና እንዲወጣ ትኩረት ሰጥቶ መሥራት ይገባል ሲሉ ተናግረዋል። የክፍለ ከተማው ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት ኃላፊ ዶ/ር ጥበቡ ደጀኔ በበኩላቸው የፀጥታ ሥራዎችን በትኩረት ለመሥራት ጥምር ኃይሉ ወንጀሎች ከመከሰታቸው በፊት የፀጥታ አዝማሚያና ዝንባሌዎችን በመቃኝት የአፍራሽ ኃይሉን እኩይ ተግባር ከስርከርስ ማከሽፍ የሁላችንም ተቀደሚ ተግባር ሊሆን ይገባል ሲሉ ገልጸዋል። የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መመሪያ አዛዥ ኮሚሽነር መኮነን አሻግሬ በበኩላቸው የፀጥታ አካላትን አስተባብሮና አቀናጅቶ የፀጥታ ሥራዎችን ለመሥራት ህዝቡን የሰላም ባለቤት በማድረግና ሰላምና ደህንነቱ ከማረጋገጥ አንፃር የተሰሩና ሊሰሩ የሚገባቸው ጉዳዮች ገልጸዋል። ተሳታፊዎች በበኩላቸው እስከአሁን የተሠሩ የፀጥታ ሥራዎች በጥሩ ደረጃ ማከናወን ቢቻልም በፀጥታ ሥራ መዘናጋት የማይጠበቅ በመሆኑ ሁሉንም የፀጥታ አካላት ሙሉ አቅም በመጠቀም ጠንክረን መሥራት አለብን ሲሉ ተናግረዋል።

image
image
image
image
ዜና | Oduu | News
በመንግስትና በግል ት/ቤቶች የሚገኙ የሰላም ክበባት ለመማር ማስተማር ሂደት ከፍተኛ ሚና እንዳላቸው ተገለፀ።

የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት ከመንግስትና ከግል ት/ቤቶች ለተውጣጡ የሰላም ክበባት አመራሮች ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደት እንዲሳለጥ ሚናቸውን እንዲወጡ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና አካሂዷል። የክፍለ ከተማው ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት ኃላፊ ዶ/ር ጥበቡ ደጀኔ በክፍለ ከተማው የሚገኙ ከ5ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ት/ቤቶች ውስጥ የሰላም ክበባት አደረጃጀትን በማጠናከር ሰላምን የማስረፅ እና የሰላም ክበባት የትምህርት ቤት ውስጣዊና ውጫዊ አዋኪ ድርጊቶችንና የቡድን ግጭትን በማስወገድ የመማር የማስተማር ሂደቱን ሰላማዊ የማድረግ እንዲሁም ተማሪዎችን በስነ-ምግባር ለማነፅ የሚያስችል የተቀናጀ ሥራ በመሰራት ላይ እንደሚገኙ ገልፀዋል። በክፍለ ከተማው ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት የህብረተሰብ አደረጃጀትና ተሣትፎ ሥራዎች አስተባባሪ አቶ አምባዬ ወ/ማርያም በበኩላቸው የሰላምን አስፈላጊነትና የተማሪዎች ስነ-ምግባርና የትምህርት ቤቶች የሰላም ክበባት አባላትና መምህራንን ጨምሮ በክበባቱ አባላት የሚሰጡት ጥቆማ አማካኝነት አዋኪ ድርጊቶች እና የቡድን ግጭት ዙሪያ አፋጣኝ እርምጃ በመውሰድ ከስጋት ነፃ የማድረግ ኃላፊነትና ተግባር መወጣት ይገባችኋል ሲሉ ባዘጋጁት የስልጠና ሰነድ በዝርዝር አቅርበዋል። የስልጠናው ተሳታፊዎች በበኩላቸው የሰላም ክበባት አባላት ተማሪዎች በትምህርት ቤቶች አካባቢ የሚገኙ አዋኪ ድርጊቶችን በመከታተል መጠቆም ፣ በባህሪ ወጣ ያሉ ተማሪዎችን የመምከር ሥራና በሰላማዊ የመማር የማስተማር ሂደት ዙርያ ውጤታማ ሥራዎችን መሥራታቸውን ገልጸዋል።

image
image
image
image
ዜና | Oduu | News
ወጣቶች ለጠንካራ ሃገረ መንግስት ግንባታ መሳካት ጉልህ ድርሻ ያላቸው በመሆኑ በሰላም ጉዳይ ከመንግስት ጋር ተቀናጅተው እየሰሩ መሆናቸው ተገለፀ::

በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ከሚገኙ ወጣቶች በወቅታዊ የሰላምና ፀጥታ ጉዳይ ዙሪያ ውይይት ተካሂዷል፡፡ መድረኩን የመሩት የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ምክትልና ፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አብነት አሰግድ የወጣቶችን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የተለያዩ እቅዶች ተነድፈው ተግባራዊ በመደረግ ላይ መሆኑን ጠቅሰው ወጣት ለሃገር ግንባታም ሆነ ለማህበረሰባዊ ተጠቃሚነት መረጋገጥ ጉልህ ሚና ያለው በመሆኑ ከመንግስትና ህዝብ ጋር ተናቦና ተቀራርቦ መስራት ይገባል ሲሉ ገልፀዋል፡፡ የክፍለ ከተማው ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት ሃላፊ ዶ/ር ጥበቡ ደጀኔ በበኩላቸው ወጣቶች በሃገረ መንግስት ግንባታ ሂደት የማይተካ ሚና ያላቸው በመሆኑ ሃገራችን የጀመረችውን የብልፅግና ጉዞ ለማስቀጠል እያደረጉት ያለውን ተሳትፎ አጠናክረው መቀጠል ይኖርባቸዋል ብለዋል፡፡ በውይይት መድረኩ የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት እስታፍ አባሎ ኮሎኔል ግርማይ የተገኙ ሲሆን የአካባቢን ሰላምና ደህንነት ለማስጠበቅ ወጣቶች እንደሁልጊዜውም የሚያደርጉትን ጥረት አጠናክረው ማስቀጠል እንዳለባቸውም በመድረኩ ተገልጿል::

image
image
image
image
ዜና | Oduu | News
በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ አስተዳደር ወቅታዊ የፀጥታ ሥራዎች ያሉበት ደረጃ ተገመገመ::

መድረኩን የመሩት የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ምክትልና ፖለቲካ ዘርፍ ሃላፊ አቶ አብነት አሰግድ ህብረተሰቡን ያሳተፈ የፀጥታ ስራ በመሰራቱ ሰላምና ደህንነቱ የተረጋገጠበት ክፍለ ከተማን መፍጠር መቻሉን ገልፀው ህዝባችንን ያሳተፈው የፀጥታ ተግባር ተጠናክሮ መቀጠል ይኖርበታል ብለዋል:: የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አደረጃጀት ዘርፍ ሃላፊ አቶ ደመቀ ዋኘው በበኩላቸው ወንጀሎች ከመከሰታቸው በፊት የፀጥታ አዝማሚያና ዝንባሌዎችን በመቃኝት የአፍራሽ ኃይሉን እኩይ ተግባር አስቀድሞ በማክሸፍ አስተማማኝ ሰላም መረጠ ተችሏል ብለዋል:: የክፍለ ከተማው ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት ሃላፊ ዶ/ር ጥበቡ ደጀኔ በበኩላቸው የፀጥታ ጥምር ኃይሉ ከተለያዩ ተቋማት ጋር በቅንጅት በመስራት የክፍለ ከተማችንን ሰላምና ደህንነት በአስተማማኝ ሁኔታ መጠበቅ እና ህዝቡ በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴው ተረጋግቶ እንዲኖር ማድረግ መቻሉን አስታውቀዋል::

image
image
image
image
ዜና | Oduu | News
ህዝቡ እራሱ የሰላሙ ባለቤት እንዲሆን በማድረግ ውጤታማ የሰላምና ደህንነት ስራ መሰራቱ ተገለፀ::

የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት እና የደንብ ማስከበር ጽ/ቤት የ2017 በዓት ዓመት አፈፃፀም እና የ2018 በጀት ዓመት እቅድን ከፀጥታ ሃይሎች፣ ከሰላም ሰራዊት አባላት እና ከሌሎች ባለድርሻዎች ጋር አወያይተዋል፡፡ የክፍለ ከተማው ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት ሃላፊ ዶ/ር ጥበቡ ደጀኔ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት እንደ መስቀል፣ ኢሬቻና መውሊድ አይነት ታላላቅ የአደባባይ በዓላትን ሰላማዊ በሆነ መንገድ እንዲከበሩ የተቀናጀና ውጤታማ ስራ መሰራቱን ጠቅሰው የሰላምን ጉዳይ የቅድሚያ ቅድሚያ ሰጥተን መስራታችንን አጠናክረን እንቀጥላለን ሲሉ ገልፀዋል፡፡ የክፍለ ከተማው ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ሃላፊ ሻምበል ኡባድ ጁና በበኩላቸው በክፍለ ከተማው ህግና ስርዓት እንዲከበር እንዲሁም ህገወጥነትን በመከላከል አበረታች ተግባራት በመከናወን ላይ ይገኛል ሲሉ ተናግረዋል:: የውይይቱ ተሳተፊ የሰላም ሰራዊት አባላት በበኩላቸው ‎የሰላም ምንጭም የሰላም ዘብም ህብረተሰቡ በመሆኑ ለሰላማችን የቅድሚያ ቅድሚያ ሰጥተን መስራታችንን እናስቀጥላለን ሲሉ ተናግረዋል:: ‎

image
image
image
image
ዜና | Oduu | News
ህጋዊ የደረሰኝ ግብይት በማስፈን የተረጋጋ የገበያ ሁኔታ ለመፍጠር በትኩረት እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ፡፡

የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ የገበያ ማረጋጋት የጋራ ግብረ-ሃይል የተረጋጋ ገበያ ከመፍጠር አንፃር እንዲሁም ከደረሰኝ ቁጥጥር እና ክትትል ጋር እየተሰራ ያለውን ስራ ገምግሟል:: በመድረኩ የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ታረቀኝ ወርቅነህ፣ የንግድ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ አብዱልዋሂድ በድሩ፣ የሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት ሃላፊ ዶ/ር ጥበቡ ደጀኔ እንዲሁም ሌሎች የክፍለ ከተማና የወረዳ አመራሮች ተገኝተዋል:: የደረሰኝ ቁጥጥርና ክትትል ስራውን በማጠናከር ህጋዊ ግብይት ማስፈን እንደሚገባ የገለፁት የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ እና የጋራ ግብረሃይሉ ሰብሳቢ አቶ ታረቀኝ ወርቅነህ የኑሮ ውድነቱን በማቃለል የተረጋጋ የገበያ ሁኔታ ለመፍጠር በትኩረት እየተሰራ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

image
image
image
image
ዜና | Oduu | News
በበጀት ዓመቱ የተሠሩ የሰላምና ፀጥታ ሥራዎች የእቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር ውይይት ተካሄደ ።

የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት በበጀት ዓመቱ የተሠሩ የሰላምና ፀጥታ ሥራዎች የእቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ከሃይማኖት አባቶች ፣ከሀገር ሽማግሌዎች ፣ከአባገዳ፣ ከነጋዴው ማህበረሰብ እንዲሁም ከተለያዩ አደረጃጀት ጋር ውይይት አካሄደ ። መድረኩን የመሩት የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ ዶ/ር ጥበቡ ደጀኔ እንዳሉት የሰላምና ፀጥታ ሥራዎች የሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች ኃላፊነትና ተግባር እንደመሆኑ መጠን ከፀጥታ አካላት ጋር በመሆን የከተማዋን ብሎም የክፍለ ከተማችንን የሰላም ደህንነት በአስተማማኝ የፀጥታ ሥራዎች በጋራ የሚሠራ መሆኑን ገልፀው ፣ በቀጣይ የሠላም ሠራዊትን አቅምና ግብዓት በማማሟላት ጠንካራ የሰላምና ፀጥታ ሥራዎች መሥራት ይገባናል ሲሉ ተናግረዋል ። በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት የፀጥታ መረጃ ቅጥር ማደራጃና ፈጣን ምላሽ ሰጪ ቡድን አቶ ዮሐንስ ወልዴ በበኩላቸው የ2017 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት፣ የመልካም አስተዳደር ሥራዎችና የ90 ቀናት እቅድ ሰነድ ለተሳታፊዎች በዝርዝር አቅርበዋል። የውይይት ተሳታፊዎች በበኩላቸው የፀጥታ ሥራዎችን የምንሠራው የአከባቢያችን ሰላም እና ደህንነት ለመጠበቅ ሁላችንም የበኩላችንን ሚና መወጣት ይገባናል ሲሉ ገለፀወል። ‎

image
image
image
image
ዜና | Oduu | News
የሰላም ሠራዊትን ማጠናከር አስፈላጊ መኾኑን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።

የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በ3ኛው የአዲስ አበባ ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ የምክር ቤት አባላት ላነሷቸው ጥያቄዎች ምላሽ እና ማብራሪያ ሰጥተዋል። ከንቲባ አዳነች አቤቤ በምላሻቸው የሰላም እና ደኅንነት ሥራዎች አበረታች መኾናቸውን ገልጸዋል። አሁንም የዝርፊያ እና የጸረ ሰላም ኀይሎች እንቅስቃሴ እንዳለ ተናግረዋል። ሕዝቡ የሰላሙ ዋነኛ ባለቤት በመኾኑ የሰላም ሠራዊቱን በቁጥር፣ በጥራት እና በብቃትም ማጠናከር አስፈላጊ መኾኑን አስገንዝበዋል። ከተማዋ የወንጀለኞች መሸሸጊያ እንዳትኾን ዘመናዊ የሴኩሪቲ መሳሪያዎች መትከል እና በሕዝብ እና በጸጥታ ኀይሎች መካከል ያለውን ቅንጅት ማሳደግ ትኩረት እንደተሰጠው አንስተዋል። በተሠራው ሥራ ከፍተኛ ውጤት እንደተመዘገበበት አብራርተዋል። ይህ ጥረት ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም አመላክተዋል። የመሬት ልማት አሥተዳደር አገልግሎቶችን ፈጣን እና ተደራሽ ለማድረግ የተጀመሩ የዲጂታል አገልግሎት ሥራዎች በጥሩ ሁኔታ ላይ መኾናቸውንም ጠቁመዋል። አሁን ባለው ደረጃ 347 አገልግሎቶችን በ"መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት" ለማስጀመር ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁን ገልጸዋል። በቀጣይም የዕውቀት እና ልምድ ልውውጥን በማስፋት ዲጂታል አገልግሎቱን ለማሻሻል እንደሚሠራ ነው ያስገነዘቡት። ከ4ሺህ በላይ መሪዎች፣ ባለሙያዎች እና ደላሎች በሌብነት እና በሙስና ወንጀል ተሰማርተው በመገኘታቸው ሕግ የማስከበር ተግባር መፈጸሙን ተናግረዋል። ይህም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ከንቲባዋ አስታውቀዋል። አገልጋይ ማገልገል ግዴታው፣ ተገልጋይም መገልገል መብቱ በመኾኑ ሙስናን መዋጋት ተገቢ እንደኾነም አጽንኦት ሰጥተዋል። የነዋሪዎችን የቤት ጥያቄ ለመመለስ በተሠራው ሥራ ከ55 ሺህ በላይ ነዋሪዎችን የቤት ባለቤት እንዳደረጉ ከንቲባዋ ገልጸዋል። በቀጣይ በጀት ዓመት የቤት ግንባታ በልዩ ትኩረት እንደሚሠራ እና መንግሥት ብቻውን መመለስ ስለማይችል ባለሃብቶችን በመሬት አቅርቦት እና ድጋፍ በመስጠት በቅንጅት እንደሚሠራ አስታውቀዋል። የኑሮ ውድነትን ለመግታት እና ሰው ሠራሽ የዋጋ ንረትን ለመከላከል የከተማ አሥተዳደሩ በድጎማ፣ በኅብረት ሥራ ማኅበራት፣ በገበያ ማዕከላት እና በእሑድ ገበያ በተመጣጣኝ ዋጋ ምርቶችን በማቅረብ፣ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ባሉ የኅብረተሰብ ክፍሎች ላይ የኑሮ ጫና እንዳይበረታ እየተሠራ መኾኑን ገልጸዋል። ይህ ተግባርም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ነው ያስገነዘቡት። ጉባኤው በከሰዓት ውሎው የ2017 በጀት ዓመት የኦዲት ሪፖርት ቀርቦለት ውይይት አድርጎበታል። በነገ ውሎው ደግሞ የዳኞችን፣ የተለያዩ ሹመቶችን እና በአዲስ የሚቋቋሙ ተቋማትን በአዋጅ እንደሚያጸድቅ ይጠበቃል። ዘጋቢ፦ አዲሱ ዳዊት የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ

image
image
image
image
ዜና | Oduu | News
የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረሃይል በወቅታዊ የሰላምና ደህንነት ዙሪያ እየተሰሩ ያሉ ተግባራትን በተመለከተ ግምገማ አካሄደ፡፡

በመድረኩ የጋራ ግብረሃይሉ አባላት፣ የፖሊስ መምሪያ የስራ ሃላፊዎችና የሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት አመራሮች በተገኙበት ሰላምና ደህንነትን ለማስከበር እየተሰሩ ያሉ ተግባራት ተገምግመዋል፡፡ የውይይት መድረኩን የመሩት የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ታረቀኝ ወርቅነህ ህብረተሰቡን ያሳተፈ የሰላምና ፀጥታ ማስከበር ስራ መሰራቱ ውጤት እየተገኘበት በመሆኑ ተጠናክሮ መቀጠል ይኖርበታል ሲሉ ገልፀዋል:: የአዲስ አበባ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ምክትል ሃላፊ አቶ ተስፋዬ ደንድር በበኩላቸው ህዝቡን የሰላሙ ባለቤት አድርጎ መስራት ተገቢ መሆኑን ገልፀው የየወቅቱን ነባራዊ ሁኔታ ታሳቢ ያደረገ የተቀናጀ ስምሪት በመውሰድ ተግባራዊ ማድረግ ይገባል ሲሉ ገልፀዋል:: የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ምክትልና ፖለቲካ ዘርፍ ሃላፊ አቶ አብነት አሰግድ በበኩላቸው ለሰላምና ፀጥታ ተግራራችን ልዩ ትኩረት በመስጠት ተቀናጅቶ መስራት ይገባል ብለዋል:: የክፍለ ከተማው ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት ሃላፊ ዶ/ር ጥበቡ ደጀኔ በዘርፉ እየተሰሩ ያሉ ተግባራትን በተመለከተ ሪፖርት አቅርበው ውይይት ተደርጎበታል::

image
image
image
image