image
image
image
image
image

የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ አስተዳደር የፀጥታ ጥምር ግብረ ኃይል ወቅታዊ የፀጥታ ሥራዎችን ገመገመ።

ታህሳስ 2, 2017
የክፍለ ከተማው የፀጥታ ጥምር ኃይሉ ሁሉም የፀጥታ ጥምር ግብረ ኃይል አባላት በተገኙበት ትኩረት በሚሹ ወቅታዊ የፀጥታ ሥራዎችን በጥልቀት ገምግሟል። መድረኩን የመሩት የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ዋና ሥራ አስፈፃሚና የጥምር ኃይሉ ሰብሳቢ አቶ ታረቀኝ ወርቅነህ ጥምር ኃይሉ የተሠሩ ወቅታዊ የፀጥታ ሥራዎችን በአግባቡ ከተለያዩ ተቋማት ጋር በቅንጅት ሥራዎችን ለሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ተልዕኮና ሥምሪት በመሥጠት የክፍለ ከተማውን ሰላምና ደህንነት በአስተማማኝ ሁኔታ መጠበቅና ነዋሪዎችን በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴው ተረጋግቶ እለት ተዕለት ተግባሩን እንዲያከናውኑ ሁላችንም ኃላፊነታችንን እንወጣ ሲሉ አሳስበዋል። የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ብርሃኑ ረታ በበኩላቸው ወቅታዊ የፀጥታ ሥራዎችን ለማከናወን ሰላምና ደህንነትን ማረጋገጥ የሚቻለው የፀጥታ ኃይሉ ከህብረተሰቡ ጋር ተቀናጅቶና ተናቦ ሲሰራ መሆኑን ጠቅሰው፤ የአፍራሽ ኃይሉን ከፋፋይ አጀንዳዎችንና ህገ ወጥ ተግባራትን በመከላከል ረገድ የሰላም ሰራዊት አባላትና ህብረተሰቡ የበኩሉን ሚና እንዲወጣ ትኩረት ሰጥቶ መሥራት ይገባል ሲሉ ተናግረዋል። የክፍለ ከተማው ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት ኃላፊ ዶ/ር ጥበቡ ደጀኔ በበኩላቸው የፀጥታ ሥራዎችን በትኩረት ለመሥራት ጥምር ኃይሉ ወንጀሎች ከመከሰታቸው በፊት የፀጥታ አዝማሚያና ዝንባሌዎችን በመቃኝት የአፍራሽ ኃይሉን እኩይ ተግባር ከስርከርስ ማከሽፍ የሁላችንም ተቀደሚ ተግባር ሊሆን ይገባል ሲሉ ገልጸዋል። የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መመሪያ አዛዥ ኮሚሽነር መኮነን አሻግሬ በበኩላቸው የፀጥታ አካላትን አስተባብሮና አቀናጅቶ የፀጥታ ሥራዎችን ለመሥራት ህዝቡን የሰላም ባለቤት በማድረግና ሰላምና ደህንነቱ ከማረጋገጥ አንፃር የተሰሩና ሊሰሩ የሚገባቸው ጉዳዮች ገልጸዋል። ተሳታፊዎች በበኩላቸው እስከአሁን የተሠሩ የፀጥታ ሥራዎች በጥሩ ደረጃ ማከናወን ቢቻልም በፀጥታ ሥራ መዘናጋት የማይጠበቅ በመሆኑ ሁሉንም የፀጥታ አካላት ሙሉ አቅም በመጠቀም ጠንክረን መሥራት አለብን ሲሉ ተናግረዋል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች