image
image
image
image
image

የጥምቀት በዓል ሐይማኖታዊ ትውፊቱ ተጠብቆ በሰላም እንዲጠናቀቅ በክፍለ ከተማው የተደረገው የቅድመ ዝግጅት ስራ የሚደነቅ ነው:: ወ/ሮ አለምፀሐይ ሽፈራው: - የአዲስ አበባ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅርጫፍ ጽ/ቤት ምክትልና ፖለቲካ ዘርፍ ሃላፊ

ጥር 21, 2017
የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ አስተዳደር የከተራና የጥምቀት በዓል አከባበር ቅድመ ዝግጅት ሥራዎችን በተመለከተ የከተማ ደጋፊ አመራሮች እንዲሁም የክፍለ ከተማና የወረዳ አመራሮች በተገኙበት ተገምግሟል:: መድረኩን የመሩት የአዳስ አበባ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ምክትልና ፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ ወ/ሮ አለምፀሐይ ሽፈራው የጥምቀት በዓል ሐይማኖታዊ ትውፊቱ ተጠብቆ በሰላም እንዲጠናቀቅ በክፍለ ከተማው የተደረገው የቅድመ ዝግጅት ስራ የሚደነቅ መሆኑን ጠቅሰው፣ በበዓሉ አከባበር ላይ በዓሉን የማይመጥኑና በህግ የተከለከሉ ነገሮችን በዓሉ ወደ ሚከበርባቸዉ ቦታዎች ይዞ አለመገኘት እና በዓሉ በድምቀት ተከብሮ እንዲያልፍ ለማስቻል አመራሩ ከፀጥታ ኃይሉ ጋር ተቀናጅቶ በመስራት ኃላፊነቱን በጥብቅ ዲሲፕሊንና በብቃት እንዲወጣ አጠንክሮ መሥራት ይገባል ብለዋል። የአዲስ ከተማ ክ/ክፍለ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ታረቀኝ ወርቅነህ በበኩላቸው በዓሉ ሰላማዊ ሆኖ እንዲከበር አስፈላጊው የቅድመ ዝግጅት ስራ ተጠናቅቆ ወደ ተግባር መገባቱን አስታውቀዋል:: የክፍለ ከተማው ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዘሪሁን ኮርሜ በበኩላቸው ወጣቶችና ህብረተሰቡ ከፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት በዓሉ በሰላም እንዲጠናቀቅ ሰፊ ስራ የተሰራ ሲሆን በዚህም ከተለያዩ የህዝብ አደረጃጀትና የፀጥታ አካላት እንዲሁም መላው ህዝባችን ጋር ውይይት መደረጉን አስታውሰው፤ ህብረተሰቡ ከአጠቃላይ ፀጥታ አካላት ጋር እጅና ጓንት በመሆን በዓሉ በድምቀት እንዲከበር የበኩሉን ሚና እንዲወጣ የሚያስችል ስራ መሰራቱን ገልጸዋል። የአዳስ አበባ ከተማ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ አወሉ መሐመድ በበኩላቸው በዓሉ ሐይማኖታዊ ሥነ ሥርዓቱንና ትውፊቱ ተጠብቆ እንዲከበር እና ለጋራ ደህንነት ሲባል የፀጥታ ኃይሉ ለሚያከናውነው የፀጥታ ስራ ህብረተሰቡ ተባባሪነቱን አጠናክሮ እንዲቀጥል አስገንዝበዋል። በመድረኩ የክፍለ ከተማው ሰላምና ፀጥታ ኃላፊ ዶ/ር ጥበቡ ደጀኔ እስካሁን የተሰሩ ስራዎችንና የወደፊት አዝማሚያዎችን የሚያስቃኝ መወያያ ሰነድ አቅርበዋል::

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች